#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ ርዕይ!

4

 

“ዓባይ ህትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ሀገራዊ ኀላፊነቱን ይወጣል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

ዓባይ ህትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ሚስጥራዊ ደረሰኝ ህትመት ለመከወን ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ይህ ሚስጥራዊ ደረሰኝ ለግብር ከፋዮች ብርሃን እና ሰላም ብቻ ያትመው የነበረ መኾኑን የተናገሩት የገቢዎች ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እና የሚኒስትሯ ተወካይ ፍቃዱ ታደሰ ደረሰኙ ለሚኒስቴሩ ወሳኝ ብቻ ሳይኾን ገንዘብም በመኾኑ በከፍተኛ ኀላፊነት የሚሠራ ነው ብለዋል።

ዛሬ የኢትዮጵያን ሁኔታ እና አቅም የሚመጥን አሠራር ለማስፋት በማስፈለጉ፣ የመልካም አሥተዳደር ችግር ለመቅረፍ፣ ፍጥነት እና ቅልጥፍናን ለማምጣት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከዓባይ ህትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ጋር ተፈራርመናል ነው ያሉት።

በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የዓባይ ህትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ቦርድ ሠብሣቢ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የሀገራችንን የግብር አሥተዳደር ሥርዓት ለማጠናከር በፌዴራል እና በክልል መስሪያቤቶች መካከል ጠንካራ ትስስርን ለመፍጠር፣ ግብር ከፋዩ በቅርበት አገልግሎት በማግኘት የተሻለ የግብር አሠባሠብ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

ተቋሙ ከዚህ በፊት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲግሪ ህትመት፣ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍሎች ሰርተፍኬት ህትመት ሲያከናውን የቆየ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በግብር ከፋይነት የብር ደረጃ ተሸላሚ መኾኑ ሥራውን በታማኝነት፣ በሚስጥራዊነት እና በብቃት እንዲወጣ መሠረት ይኾነዋል ብለዋል።

ዓባይ ህትመት እና የወረቀት ፓኬጂንግ ክልላዊ ብቻ ሳይኾን ሀገራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት ጠንክሮ በመሥራት የተሰጠውን ኀላፊነት በአግባቡ እንደሚወጣም ቃል ገብተዋል።

የሚስጥራዊ ደረሰኙ የግብር ከፋዩን ሙሉ መረጃ በኪውአር ኮድ የያዘ፣ በዐይን የማይለዩ የሚኒስቴር መስሪያቤቱን መረጃ የያዘ፣ ያለ ካርበን 3 ገፆች ላይ በአንድ ጊዜ መፃፍ የሚያስችል አቅም ያለው እና በግልጽ የሚታዩ አስፈላጊ መረጃዎች የሚታተሙበት ነው።

ፋብሪካው በቀን 160 ሺህ መጻሕፍትን የማተም አቅም እንዳለው ከመድረኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#አሚኮ ​#Ethiopia🇪🇹​ #ዓባይህትመት

#አዲስ_አበባ #መስከረም_22_2019_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ፦አንዱዓለም መናን

‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹
Next article#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!