
“የኢትዮጵያን ሰላም እና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነን” የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከከተማ አሥተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አስራት ሙጨ የመንግሥት ሠራተኞች በሙያቸው ሕዝብን በአግባቡ ማገልገል እና ለልማት እና ለሰላም ማንቃት ይገባል ብለዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ጊዜው ታከለ ሕዝቡ በ2018 ዓ.ም ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ አካሂዷል ብለዋል። የሕዝብን የመልማት ጥያቄ የሚመልስ አዲስ መንግሥት መመስረት እንደተቻለም ተናግረዋል።
ይህን ሀገራዊ ስኬት ለማይፈልጉ አካላት ጆሮ መስጠት አያስፈልግም ነው ያሉት። ሰላምን እያስጠበቁ በሙሉ ልብ ልማትን ማካሄድ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የመንግሥት ሠራተኞች የአማራ ሕዝብ ብሎም ኢትዮጵያን ማኅበራዊ ረፍት ለመንሳት የሚጥሩ አካላት መኖራቸውን አበክረው በመረዳት ለሰላምና ለልማት እንደሚሠሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ ምንጊዜም ዝግጁ እንደኾኑም አረጋግጠዋል።
#አሚኮ #ሰላም #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_22_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ አዲኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
