የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባዔውን እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በከሰዓት ጉባዔው የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ሹመት አጽድቋል።

በዚህም፦

አቶ ከፍ ያለው ሙላቴ:- የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ እና ውኃ ሃብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

አቶ አበራ ፈንታው :-የሰው ሃብት እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ወይዘሮ እመቤት ከበደ:- የመንግሥት ወጪ አሥተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ወይዘሮ አድና ምኅረቱ :- የሴቶች፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ወይዘሮ ሃናን አብዱ:- የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

አቶ ደሴ መኮንን:- የሕግ እና ፍትሕ አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

አቶ አራጌ ይመር:- የከተማ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኾነው ተሹመዋል።