አዲስ አበባ የ2026 የከተሞች ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ሽልማት ተሸለመች።

2

 

አዲስ አበባ የ2026 የከተሞች ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ሽልማት ተሸልማለች።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ አዲስ አበባ የ2026 የከተሞች ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ሽልማትን (2026 Global Award for Sustainable Development in Cities) ማግኘቷ፣ በከተማዋ የታየውን እድገት፣ ዘላቂ ልማትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ የሚያረጋግጥ በመኾኑ ለኢትዮጵያ ታላቅ ኩራት ነው ብሏል።

ይህ ደግሞ ወደፊት ለመመልከት መልካም አጋጣሚ ነው። የእያንዳንዱን ከተማ ልዩ ታሪክ፣ ቅርስና ማንነትን እየጠበቅን ዘመናዊ፣ አካታችና ዘላቂ ከተሞችን መገንባታችንን መቀጠል ይኖርብናል። የከተማ ልማት ከመሠረተ ልማት በላይ ነው። የከተሜነት ባሕልን ማሳደግ፣ ጥራት ያላቸው የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን መፍጠር እና ከተሞቻችንን ለመኖርና ለመሥራት የተሻሉ ቦታዎች ማድረግ ማለት ነው።

ራዕያችን ከአዲስ አበባ ባሻገር ሊሰፋ ይገባል። ከሐረር እስከ ባሕር ዳር፣ ከሐዋሳ እስከ ጅማ፣ ከአርባ ምንጭ እስከ ድሬዳዋ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ከተማ የዘላቂ ከተማ ልማት ማሳያ የመኾን አቅም አለው ነው ያለው።

ዛሬ አዲስ አበባ፤ ነገ ደግሞ ለእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ከተማ አዲስ ምዕራፍ። ከታሪካቸው ሳይነጠሉ የወደፊቱን ጊዜ የሚመጥኑ ከተሞችን እንገንባ ብሏል።

Previous article🌾 በአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የተመዘገቡ ስኬቶች እና የለውጥ ጉዞ!
Next articleየመስኖ ልማት እና የአርሶ አደሮች ተስፋ በሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ!