#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ ርዕይ! ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግሥት ሠራተኛው ሚና!

4
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በዘላቂ ሰላም እና በመልካም አሥተዳደር ዙሪያ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል መንገድ ኤጀንሲ ምክትል ኀላፊ አስራቴ አለኸኝ የመንግሥት ሠራተኛው ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍናን በማሻሻል የሚነሱ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት እንዳለበት አሳስበዋል።
ለሀገር ሰላም እና አንድነት በጋራ እና በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ስለሺ ተመስገን የመንግሥት ሠራተኛው በየአካባቢው ለሰላም መስፈን ግንባር ቀደም መኾን እንዳለበትም ገልጸዋል።
በከተማዋ የሚነሱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። የታቀዱ የልማት ተግባራትን በስኬት ለመፈጸም የሠራተኛው ሚና ከፍተኛ መኾኑን አብራርተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የመንግሥት ሠራተኞች በበኩላቸው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። ለሰላም መስፈን የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከተማዋን የሚመጥኑ የልማት ሥራዎችን ማፋጠን፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት እና ለሌሎችም የኅብረተሰብ ጥያቄዎች መንግሥት ትኩረት መስጠት እንዳለበት አንስተዋል።
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ ርዕይ!
Next article#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ ርዕይ!