ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ

21
ከፈተናዎች ማዶ የተበሰረ አዲስ ተስፋ፤ የአማራ ክልል የመንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ድምፅ ማክበር።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ተአማኒ እና ነጻ ምርጫ ማካሄዱን ተከትሎ ዛሬ የክልሉ ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
ይህ ታሪካዊ ዕለት ክልሉ የገጠሙትን ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች በጽናት እና በጥበብ ተቋቁሞ ያለፈበት ሕያው ማሳያ ነው።
ክልሉ ያሳየው ይህ ውጤታማ የመንግሥት ምሥረታ ሂደት የወቅቱ መሪዎች ያላችውን ጠንካራ አሥተዳደራዊ ብቃት፣ ጽናት፣ ቁርጠኝነት እና ለሕዝብ ፍላጎት የመገዛት ጥንካሬን በግልጽ ያሳየ ሁነኛ ምስክር ነው ማለት ይቻላል። ይህ ስኬት የመንግሥት ምሥረታ ብቻ ሳይኾን በፈተናዎች ውስጥ አልፎ የሕዝብን ድምፅ ማክበር መቻልም ነው።
በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተጣለ እምነት ለክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት መንገድ የሚከፍት ነው። የክልሉ ሕዝብ ወደፊት ለሚኖረው የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዞ የጣለውን ተስፋ ያደሰ ታላቅ ክስተትም ነው።
የዛሬው የመንግሥት ምሥረታ ለክልሉ ዘላቂ የሰላም ግንባታ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት ትልቅ አቅም የሚፈጥር አዲስ ምዕራፍም ነው!
በቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!
Next article#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!