#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!

8
“በክልሉ ሰላም እና የፖለቲካ መረጋጋት እንዲመጣ ይሠራል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ በድጋሜ ሹሟል።
ከሹመታቸው በኋላ መልዕክት ያስተላለፉት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ የከፈተ መኾኑን ገልጸዋል። ሕዝቡ የዳበረ የሀገረ መንግሥት ምሥረታ ታሪክ ያለው እና ሰላም ወዳድ መኾኑን ለዓለም ያስመሰከረበት መኾኑን ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ በድጋሜ ሹመት ስለሰጣቸው ምሥጋና አቅርበዋል። በክልሉ ሰላም እና የፖለቲካ መረጋጋት እንዲመጣ ጠንክረው እንደሚሠሩም ገልጸዋል። ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ክልሉን ለልማት የተመቸ ለማድረግ እንደሚሠራም ተናግረዋል።
የጸጥታ እና የፍትሕ አካላት የዜጎችን ደኅንነት በዘላቂነት ማረጋገጥ ይሠራል ነው ያሉት። በተቋሙ ላይ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።
ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት እና የሃሳብ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሠራም ተናግረዋል። አብሮነትን ለማጠናከር ገዢ ትርክት ላይ ይሠራልም ነው ያሉት። ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመውጣት እና ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሠሩም ተናግረዋል።
የሚቀጥሉት ዓመታት ግጭት የራቀባቸው እና ሰላም የተረጋገጠባቸው እንዲኾኑ በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል። ሃብት በሚፈጥሩ እና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ በሚያሻሽሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
Next articleትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ