#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!

20
ክልሉን ወደ ከፍታ ለመውሰድ እየተጉ ያሉት ጠንካራውን መሪ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን በጨረፍታ።
ለአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው የተሾሙት አቶ አረጋ ከበደ ለጋስ የትውልድ ቦታቸው መሥራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ ነው።
ርእሰ መሥተዳድሩ በትምህርት ዝግጅታቸው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በልማት አሥተዳደር፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን አግኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከወረዳ እስከ ዞን ባሉ መዋቅሮች በተለያዩ ኀላፊነቶች ሲሠሩም ቆይተዋል። የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኾነውም ሠርተዋል።
በቀድሞ አጠራሩ የአማራ ክልል ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ፣ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት እና የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ በመኾን በውጤታማነትም መርተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከነሐሴ 19/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦሥት ዓመታት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር በመኾን ሕዝባቸውን በታታሪነት፣ በቅንነት እና በታማኝነት ሲያገለግሉም ቆይተዋል።
የአማራ ክልል ሕዝብን ካለበት ችግር አውጥቶ ወደከፍታ ለመውሰድም እየተጉ ያሉት እኝህ ጠንካራ መሪ እየተካሄደ ባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምሥረታ ጉባኤ ምክር ቤቱ በድጋሚ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ ሹሟቸዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!
Next article#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ