የአማራ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተሿሚዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። ምክር ቤቱም የቀረበውን ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ

ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ

ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ

አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ኾነው ተሹመዋል።