
“የተጣለብንን ኀላፊነት የምንወጣው በአንድነት እና በትብብር ነው” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬን በድጋሚ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አድርጎ ሰይሟል። ይሄን ዕድል ድጋሜ ስላገኘሁ አመሠግናለሁም ብለዋል።
ዋና አፈ ጉባኤዋ ይሄን ትልቅ ኀላፊነት በአግባቡ እንድወጣ የምክር ቤት አባላት እገዛ እንደማይለየኝም እተማመናለሁ ነው ያሉት። የክልሉን ሕዝብ ችግር የሚቀርፉ ሕጎችን እናጸድቃለን፣ መፈጸማቸውንም እንከታተላለን ብለዋል።
ለምክር ቤት አባላት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የተሻለ ሥራ እንሠራለንም ነው ያሉት። ብዝኀነት እንዲረጋገጥ፣ የሃሳብ ብዝኀነት እንዲከበር እንሠራለን ያሉት አፈጉባኤዋ የተጣለብንን ኀላፊነት የምንወጣው በአንድነት እና በትብብር ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
