#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!

29
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው ተሾሙ።
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው ተሹመዋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባዔውን ማካሄዱን ጀምሯል።
ምክር ቤቱ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ በድጋሜ ሹሟል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፈታኝ የጸጥታ ችግር በገጠመው ወቅት ኀላፊነት ወስደው ክልሉ እንዲረጋጋ ያደረጉ ብርቱ መሪ መኾናቸው ተገልጿል።
በእርሳቸው የመሪነት ዘመን ክልሉን ከፈታኝ የጸጥታ ችግር አውጥተው ወደ ተረጋጋ ሰላም እንዲመለስ፣ በርካታ የልማት ሥራዎች እንዲሠሩ ያደረጉ መሪ ናቸው።
ክልሉ በፈተና ውስጥ ኾኖ የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ በማቀድ ከግጭት አዙሪት እና ከድህነት እንዲወጣ የሚያስችሉ ሥራዎችን ሠርተዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#ባሕር_ዳር፡ መስከረም 21/2019 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!