
“የአቅርቦት ሰንሰለትን በፍጥነት የማድረስ ብቃት፤ የምሥራቅ ዕዝ አዲሱ ስኬት” የምሥራቅ ዕዝ ኮር የሎጀስቲክስ ክፍሎች የሠራዊቱን ዝግጅት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘቡ መኾኑን በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የመከላከያ ሠራዊት የሥራ ኀላፊ የኾኑት ኮሎኔል መንገሻ ሞላ ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ሕግ የማስከበር ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ያለው የምሥራቅ ዕዝ ኮር የሠራዊቱን የውጊያ ዝግጅት እና ቁመና የሚያጠናክሩ ዘርፈ ብዙ የሎጀስቲክስ እና የድጋፍ ሥራዎችን በስኬት እያከናወነ እደሚገኝ ነው የገለጹት።
ኮሩ የተሰጠውን ሀገር አቀፍ ግዳጅ ያለማቋረጥ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመወጣት እንዲቻል የሰንሰለት አቅርቦቱ ያለ ምንም መዘግየት ወደሚፈለገው እንዲደርስ እየተሠራ እንደኾነ ነው የተናገሩት። የሎጀስቲክስ ክፍሎች የተለያዩ ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት።
በግንባር የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች የሠራዊቱን ጤንነት በዘላቂነት ለመጠበቅ የቅድመ-መከላከል እና እንክብካቤዎችን በመስጠት፤ የንጽሕና አጠባበቅ ግንዛቤዎችን በማስፋ እና ፈጣን ሥርዓትን በመዘርጋት አመርቂ ውጤቶችን ማምጣታቸውንም አስረድተዋል ።
መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
