“የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

5

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነሥርዓት መካሄዱን ገልጸዋል።

ሥነ ሥርዓቱ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ፣ መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በመላው ምሥራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊ እና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን መሠረት ለመጣል ትልቅ እርምጃ መኾኑን የሚያረጋግጥ ሁነት ነው ብለዋል።
‎
‎በአህጉራችን የምትገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ሥራ ፈጣሪዎች፤ በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት ልታደርጉ፣ ባለን አቅም እና የጋራ ጸጋ እምነት ሊኖራችሁ፣ አህጉራዊ መፃኢ እድላችንን የሚወስኑ ለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶችን ልትገነቡ ይገባል ነው ያሉት።
‎
‎የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ🇪🇹

Previous articleለትልቅ ሀገር ትልቅ ሕዝብ ታላቅ ርዕይ መሠረቱ ዘላቂ ሰላም እና ጸጥታን ማረጋገጥ ነው።