ለትልቅ ሀገር ትልቅ ሕዝብ ታላቅ ርዕይ መሠረቱ ዘላቂ ሰላም እና ጸጥታን ማረጋገጥ ነው።

3

 

በደሴ ከተማ አሥተዳደር ከንግዱ ማኅበረሰብ ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ በከተማዋ የሚገኘውን የሰላም እና ልማት ለማስቀጠል እና የከተማዋን ብሎም የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ የጋራ ግንዛቤ እና ቅንጅት መፍጠር እንደሚገባም ተገልጿል።

አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የንግዱ ማኅበረሰብ አካላት እንዳሉት ሰላም ከሌለ ነግዶ ማትረፍ አይቻልም። አሁን የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማጽናት ከመንግሥት ጋር በትብብር እንሠራለን ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የደሴ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ ዘላቂ ሰላም እና ጸጥታን ማረጋገጥ ለንግድ እና ለኢኮኖሚ ዕድገት መነሻ ወሳኝ መኾኑን ጠቁመዋል።

በውይይት መድረኩ የንግዱ ማኅበረሰብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ማዕከል በመኾኑ ከመንግሥት ጋር በትብብር ለዘላቂ ሰላም መሥራት እንደሚገባም ተገልጿል።

#ሰላምና_ልማት #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ደሴ #መስከረም_20_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:-ደምስ አረጋ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የባሕር በር ጥያቄን መከልከል አይቻልም”
Next article“የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)