
የመደመር መንግሥት መሪዎች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለሁለንተናዊ ብልጽግና – ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያለው መሪ ያስፈልገዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ብልጽግና፣ ባሕላዊ እና ሞራላዊ ብልጽግና የተሸመኑበት ብልጽግና ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መሪዎች ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያስፈልገዋል፡፡ በአካል የዳበረ፣ በሞራል የጠነከረ፣ በዕውቀት የተሳለ፣ በጥበብ የበሰለ እንዲኾን ይጠበቅበታል፡፡ በተለይም በሀገር ፍቅር ስሜት እና በሕዝብ ተቆርቋሪነት መንፈስ ግዴታዎቹን እንዲወጣ የሀገር አደራዋ ጥብቅ ነው ብለዋል።
ወታደራዊ ሳይንስ፣ ልምድ እና ሕይወት የሰውን ልጅ ዓላማ እና ሰብእና በመቅረጽ ረገድ ተወዳዳሪ እንደሌለው ገልጸዋል። የሰው ልጅ በአካልም፣ በመንፈስም፣ በሥነ ምግባርም፣ በአፈጻጸምም ዲሲፕሊናዊ እንዲኾን በማስቻል ለዘመናት ትውልድን ሲያዘጋጅ ኖሯል ነው ያሉት። ውጫዊ እና ውስጣዊ ማንነቱ የሠመሩለት ሰብእና በመቅረጽም ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል፡፡ ግዳጅን በብቃት መፈጸም፣ በዐርበኝነት መንፈስ አገልግሎት መስጠት፤ የሥራ ዲሲፕሊንን መቅረጽ፤ የጋራ ግብን በጋራ ማሳካት፤ ወትሮ ዝግጁነት፤ በተዋረድ መሪን ማፍራት፤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት፤ ከላይ እስከ ታች በመናበብ ዓላማን መፈጸም እና የመሳሰሉት ከወታደራዊ ሳይንስና ልምድ ሊወሰዱ የሚችሉ ዕሴቶች ናቸው ብለዋል።
የመደመር መንግሥት መሪዎች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ የመደመር ሥልጣኔ ታላቁ ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል፣ ከወታደራዊ ሳይንስ እና ሕይወት የምንቀስማቸው ዕውቀቶች፣ ክሂሎቶች እና ልምዶች አሉን ነው ያሉት።
በተለይም ደግሞ በአንድ ሰዋሰው መግባባት፣ ሥነ ምኅዳርን በሚገባ መጠቀም፤ በተከታታይ ሕዝብን ለዓላማና ለተግባር ማነጽ፤ ለሕዝብ የገባነውን ቃል በሚገባ አከናውኖ መጨረስ፤ ከታች እስከ ላይ ያለውን መዋቅር ለሀገራዊ ዓላማ ማሣለጥ፤ ሀገርን በባለ አደራነት መምራት፤ ለምንምና ለማንም የማትበገር ጽኑ ሀገር መገንባት፤ ተተኪ ትውልድን ማፍራት እና የሀገርን ደኅንነት ምንጊዜም ማረጋገጥ የሚሉትን የስትራቴጂውን ሐሳቦች በተገቢው መንገድ ለመረዳትም ኾነ ለማስፈጸም ወታደራዊ ሥልጠናው የማይናቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን ነው ያሉት።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
