
በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር የማግኘት ሕጋዊ መብት አላቸው። የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ብሩክ ኀይሉ የባሕር ጠረፍ ያላቸው ሀገራት የባሕር በር የሌላቸውን ወንድም ሀገራት የመጠቀም መብት ሊከለክሉ አይችሉም ብለዋል።
ይህን ማድረግም በቀጥታ ዓለም አቀፍ ሕግን መጣስ እንደኾነ ነው የተናገሩት። በዚህም መሠረት እንደ ኤርትራ ያሉ የባሕር ጠረፍ ያላቸው የጎረቤት ሀገራት በፖለቲካዊ አለመግባባቶች ምክንያት ብቻ የኢትዮጵያን ሕጋዊ የባሕር በር ጥያቄ እና ፍላጎት ሊከለክሉ እንደማይችሉ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ሲፋጠን የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። ይህ ደግሞ ሀገሪቱ የራሷን የወደብ መሠረተ ልማት እንድትገነባ እና እንድታስፋፋ ዕድል ይሰጣል ነው ያሉት።
ይህ ሁኔታ በሕዝቡ እና በመንግሥት ላይ ትልቅ የሥነ-ልቦና ጫና፣ የደኅንነት ስጋት፣ የሀገሪቱ የወደፊት ሕልውና በሌሎች ሀገራት እጅ የመውደቅ ስጋት እንደሚፈጥር ፕሮፌሰሩ አንስተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
