ለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ የተበሠሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች

11
🏔️
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኀይል ወደ ማመንጨት መሸጋገሩን ተከትሎ ኢትዮጵያን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ፣ ቴክኖሎጂ እና ሎጂስቲክስ ማዕከልነት የሚያሸጋግሩ የ30 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በጉባ ሰማይ ሥር ይፋ የተደረጉት ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት እና በማስገኘት የኢትዮጵያን ከፍታ የሚወስኑ ናቸው። ከወሳኞቹ ፕሮጀክቶች መካከል የነዳጅ ማጣሪያ እና የጋዝ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክለር ማበልጸጊያ ይገኝበታል።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአቪዬሽን እምብርት የሚያደርገው የቢሸፍቱ አውሮፕላን ማረፊያም ሌላኛው መልኳን ለዓለም የገለጠ ፕሮጀክት ነው።
የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጠው ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና የቤት እጥረትን በመቅረፍ ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥረው የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታም የሀገሪቱ ርዕይ የዜጎችን ፍላጎት በማሟላት ላይ ያተኮረ ለመኾኑ የሚያረጋግጡ ናቸው።
በጉባ የተበሰሩት እነዚህ ፕሮጀክቶች ከርዕይ ወደ ተግባር በመቀየር ኢትዮጵያን ከውጭ ጥገኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት፣ ዓለም አቀፍ ልዕልና እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያሻግሩ የዘመኑ የዕድገት ሞተሮች ናቸው።
✍️ በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ለታላቅ ርዕይ የሚገባ ቀልጣፋ አገልግሎት።
Next articleለትልቅ ሀገር ትልቅ ሕዝብ ታላቅ ርዕይ ኀላፊነታቸውን እንደሚወጡ የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።