ለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ለታላቅ ርዕይ የሚገባ ቀልጣፋ አገልግሎት።

6
ለተከበረችው እና ለታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ የሚመጥነው ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት በኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል።
በፌዴራል የሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ የተዘበራረቁ እና ቢሮክራሲ የተሞሉባቸውን ሂደቶች በአንድ ጥላ ስር በማሠባሠብ የዜጎችን እንግልት፣ ጊዜ እና ወጭ አስቀርቷል ይላሉ።
ይህ ማዕከል ተገልጋዮችን ከተለያዩ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር የሚወስደውን ጊዜ እና ጉልበት በማዳን፣ አገልግሎቱን ፈጣን፣ ግልጽ እና ቀልጣፋ አድርጎታል ነው ያሉት።
ይህ ዲጂታል አሠራር የኢትዮጵያን ሕዝብ ባሕል እና እንግዳ ተቀባይነት ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር ለአገልግሎት ፈላጊዎች ክብርን ሰጥቷልም ብለዋል።
በመሶብ ማዕከላት አማካኝነት ሙስና እና ብልሹ አሠራሮች እየተቀነሱ፣ የመንግሥት ሥራዎች በሥርዓት እና በታማኝነት እየተከናወኑም ይገኛሉ።
በአሚናዳብ አራጋው
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleኢትዮጵያ በልማት እና በሕዝቦቿ አንድነት ታላቅነቷን እያጸናች ትገኛለች።
Next articleለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ የተበሠሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች