ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ

7
የንግዱ ማኅበረሰብ ለሰላም፣ ለሀገር አንድነት እና ለሕጋዊ የንግድ ሥርዓት መከበር በትብብር እየሠራ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በሰላም፣ በልማት፣ እና በሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ማስፈን ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በውይይቱ ወቅት የአማራ ክልል መንገድ ኤጀንሲ ምክትል ሥራ አሥኪያጅ አስራቴ አለኸኝ የንግዱ ማኅበረሰብ ሕግን አክብሮ በመሥራት ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል።
ነጋዴዎች ግብርን በአግባቡ ከመክፈል እና ከሕገ ወጥ አሠራር ራሱን ከመጠበቅ ባለፈ የአካባቢውን ሰላም እና ልማት በማረጋገጥ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ስለሺ ተመስገን በበኩላቸው የንግድ እንቅስቃሴው እንዲጠናከር እና ልማቱ እንዲፋጠን የንግዱ ማኅበረሰብ ከከተማ አሥተዳደሩ ጋር በትብብር መሥራት እና ለፀጥታ ኃይሎች ደጀን መኾን እንደሚገባውም አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ነጋዴዎች በበኩላቸው፣ የንግድ ሥራን በነፃነት እና በመረጋጋት ለማከናወን ሰላም የመጀመሪያው መስፈርት መኾኑን አንስተዋል።
በመኾኑም በአሁኑ ወቅት የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማስጠበቅ እና የከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን ከከተማ አሥተዳደሩ ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መኾናቸውንም አረጋግጠዋል።
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ኅብረተሰቡን ከኑሮ ውድነት የመታደግ እና ሰላምን የማስከበር ሚናችንን አጠናክረን እንቀጥላለን”
Next articleኢትዮጵያ በልማት እና በሕዝቦቿ አንድነት ታላቅነቷን እያጸናች ትገኛለች።