ዘላቂ ሰላምን ማጽናት እና የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል ይገባል።

4
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይቷል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ በከተማዋ ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከማኅበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። የማኅበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያደናቅፉ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን ሴራ ማክሸፍ ይገባል ነው ያሉት። ለዚህም ሕዝቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ መወጣት እንዳለበትም አንስተዋል።
​የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ሰላምን አጥብቆ የሚፈልግ እና ሰላም ወዳድ ነውም ብለዋል። አሁን ላይ አስተማማኝ ሰላም መኖሩን አመላክተዋል።
ለዚህም ማሳያው ትናንት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል የእግር ኳስ ጨዋታ እና ስኬት ነው ብለዋል።
አሁንም ሕዝቡ ለሰላም ዘብ በመቆም ይህንን መልካም ገጽታ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አስገንዝበዋል። በጋራ እየተግባባን፣ ሕዝቡ የድርሻውን በመወጣት ልማቱን እና ሰላሙን በዘላቂነት ማስጠበቅ አለበት ነው ያሉት።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች ብለዋል። በተሠሩት የልማት ተግባራት ተጠቃሚ መኾናቸውንም ተናግረዋል። ዘላቂ ሰላምን ማጽናት እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል።
በሥራውድንቅ ደሳለው
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ጉባኤው የክልሉን የፍትሕ ሥርዓት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር መልካም ተጽዕኖ ይኖረዋል” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next article“ኅብረተሰቡን ከኑሮ ውድነት የመታደግ እና ሰላምን የማስከበር ሚናችንን አጠናክረን እንቀጥላለን”