
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከግዙፍ የውኃ እና የኮንክሪት ግንባታ ባለፈ የኢትዮጵያን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ፣ የሉዓላዊነት ክብር እና የመፈጸም አቅም አንድምታ ማሳያ ነው።
የግድቡ በስኬት መጠናቀቅ ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ዘርፈ ብዙ የዲፕሎማሲ ጫናዎች፣ የፋይናንስ ማነቆዎች እና እጅግ ውሥብሥብ የነበሩ የቴክኒክ ፈተናዎችን በብልሃት ተሻግራ የራሷን የተፈጥሮ ጸጋ የማልማት ሉዓላዊ መብቷን በተግባር ያረጋገጠችበት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የሕዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ ካለመች እንደምትደርስ፣ ከጀመረች እንደምትጨርስ በተግባር ያረጋገጥንበት ህያው ምስክር ነው” በማለት አይበገሬነት የኢትዮጵያ መልክ መኾኑን ተናግረዋል።
በጉባ ላይ የተመዘገበው ድል የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ሳይጎዳ በፍትሐዊነት ማልማት እንደሚቻል ለዓለም ያሳየ ነው። የኢትዮጵያውያንን የማይበገር መንፈስ ያንጸባረቀ እና የውስጥ አንድነትን በማጠናከር ለቀጣይ ትውልድ የሚወረስ የብልጽግና መሠረት መኾኑንም አንስተዋል።
በጠቅላላው ሕዳሴ ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር ታላቅ ሕዝብ እና ታላቅ ራዕይ ያላት ሀገር መኾኗን በዓለም አደባባይ ከፍ አድርጎ ያሳየ የዘመኑ ታላቁ የድል ሐውልትም ነው።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
