
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከሠራቻቸው ውጤታማ ሥራዎች መካከል የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ አንደኛው ነው።
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዕዳ ጫናን በመቀነስ እና የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ተጨባጭ ውጤት እያሳየ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የዕዳ ጫናን በመቀነስ እና የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል ብለዋል።
የዕዳ ማሻሻያ ስምምነቱ በስኬት መጠናቀቁ የፊስካል አና የውጭ ምንዛሬ ጫናን የሚያቀል መኾኑን ገልጸዋል። የካፒታል ገበያ ልማት፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና የውስጥ ገቢ አሠባሠብ ማደግ የሀገሪቱን ዘላቂ የፋይናንስ አቅም እያጠናከሩት መኾናቸውንም አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ከሪፎርሙ በፊት የነበረው ዓመታዊ አማካይ የዋጋ ንረት በተወሰዱ የተቀናጁ የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲ እርምጃዎች ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን አብራርተዋል።
በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ የመስኖ እና የኩታገጠም እርሻ ሥራዎች፣ ኢትዮጵያን ከስንዴ አስመጭነት ወደ ራስ አቅም ያሸጋገራት የብሔራዊ የስንዴ ፕሮግራምን ጨምሮ የምግብ አቅርቦትን በማሳደግ ለዋጋ ንረቱ መረጋጋት ዋና ምክንያት መኾናቸውን ገልጸዋል።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
