አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።

5

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት ምሥረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኀላፊ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ባለፉት ዓመታት የደሴ ከተማ አሥተዳደርን በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነት መርተዋል። በመሪነት ዘመናቸውም በደሴ ከተማ ውጤታማ ሥራዎችን ሠርተዋል።

በከተማዋ የረጅም ዓመታት የሕዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ፣ ከተማዋ ታሪኳን ጠብቃ እንድትዘምን እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል ስኬታማ ሥራዎችን ሠርተዋል።

ዛሬ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሹመዋል።

#ታላቅ_ሀገር #ታላቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

Previous articleቃል በተግባር በጣና ዳርቻ፦ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም
Next articleለትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ራዕይ የሚገባ የባሕር በር🇪🇹