ቃል በተግባር በጣና ዳርቻ፦ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም

5

 

በጣና ሐይቅ ማደሪያ ባሕርዳር በግርማ ሞገስ የቆመው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከስፖርታዊ ማዕከልነት እጅግ የዘለለ ትርጉም አለው። ስታዲየሙ ታላቅ ሀገር እና ሕዝብ የሰነቁትን የረጅም ጊዜ የመሠረተ ልማት ራዕይ እና የመንግሥትን ጠንካራ የፕሮጀክት አፈጻጸም አቅም የሚያሳይ ነው።

💎 የዘመናዊነት እና የጥራት ማማ፦

ከ50 ሺህ በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ስታዲየሙ የካፍ እና የፊፋ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ እንዲያሟላ ተደርጎ ከፍተኛ የደረጃ ማሻሻያ ተደርጎለታል።

የሜዳውን የውኃ መቋጠር ችግር በዘላቂነት ለማስወገድም ዲዛይኑ ተስተካክሎ፣ አፈሩ ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ ፈጣን የውኃ ማፋሰሻ ሥርዓት ተዘርግቶለታል። ከፍተኛ ጥራት ያለው ሳርም ምቾት እና ውበት እንዲላበስ አድርጎታል።

የተመልካች ወንበሮቹም በፀሐይ እና በብርድ የማይሞቁ እና የማይቀዘቅዙ ኾነው በልዩ ጥራት የተዘጋጁ ናቸው። ዘመናዊ የእንግዶች ( ቪ.አይ.ፒ) ቦታዎች፣ አሳንሰሮች እና ደረጃቸውን የጠበቁ የመለማመጃ ሜዳዎች ተሟልተውለታል።

🏆የመንግሥት ቁርጠኝነት እና የተግባር ስኬት፦

ስታዲየሙን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት የክልሉ መንግሥት ቁርጠኝነት ከፍተኛ እንደነበር የክልሉ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥት አስፈላጊ ሥራዎችን በፍጥነት በማሟላት እና አስቀድሞ በካፍ የተሰጡ ማስተካከያዎችን በጥንቃቄ በማረም፣ ስታዲየሙ ዳግም ዕውቅና እና ፈቃድ እንዲያገኝ ሰፊ ሥራ መሠራቱን አስታውሰዋል።

ለዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የካፍን መስፈርት የሚያሟላ ሜዳ በማጣት ከሀገር ውጭ እንዲጫወት ያስገደደውን አሳዛኝ ክፍተት ለመዝጋት የተወሰደው እርምጃ ፍሬ አፍርቷል። ይህም ጠንካራ የመፈጸም አቅም ሲኖር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜ እና ጥራት ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር አረጋግጧል።

🚀 የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ሞተርነት

ግዙፉ ሀገራዊ ሀብት የስፖርት ውድድሮችን ከማስተናገድ አልፎ ሁለገብ የንግድ ሱቆችን፣ ካፌዎችን እና ሬስቶራንቶችን አቅፎ አካቷል። ይህም የአካባቢው ኅብረተሰብ ዘመናዊ መዝናኛ እንዲያገኝ የሚያስችለው ነው።

ለዓለም አቀፍ ክለቦችም የልምምድ ማዕከል በመኾን እና የባሕር ዳርን የቱሪዝም ስበት ከፍ በማድረግ ለአካባቢው ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

🌟 የብሩህ ተስፋ እና የታላቋ ኢትዮጵያ ራዕይ፦ 🇪🇹

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የውበት እና የግርማ ሞገስ ተምሳሌት ብቻ አይደለም። ቁርጠኝነት እና ተቋማዊ ቅንጅት ሲኖር የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ የሚያደርጉ አሻራዎችን ማኖር እንደሚቻል የሚያሳይ አንጸባራቂ ሃብትም ነው።

የስታዲየሙ ፕሮጀክት ስኬት መንግሥት ይህንን የተግባር ልምድ በሌሎችም ቁልፍ የልማት ዘርፎች ላይ በመድገም የታላቂቱን ኢትዮጵያ ራዕይ ዕውን ማድረግ እንደሚችል የሚያመላክት ብሩህ ተስፋ ነው።

#ታላቅ_ሀገር_ታላቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ #አሚኮ ኢትዮጵያ🇪🇹

‎#AMECO #Football #BahirDar_International_Stadium🏟️

#ባሕር_ዳር #መስከረም_20_2019_ዓ_ም

በስማቸው አጥናፍ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleመሠባሠቢያ ቤታችን፤ ደምቆ መታያ ውበታችንን እንጠብቅ።
Next articleአቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።