ለክልሉ ሰላም በጋራ መቆም ያስፈልጋል።

4
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሐመድ (ዶ.ር) ባለፉት ዓመታት ከሕዝቡ ጋር በጋራ በተሠሩ የልማት እና የሰላም ማስከበር ተግባራት ለውጦች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ ሁለንተናዊ ተግባራት ተሠርተዋል ብለዋል። እነዚህን የልማት እና የሰላም ጉዳዮች ከሕዝቡ ጋር በመኾን በቀጣይም ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።
“ለሕዝብ እናስባለን” እያሉ የሕዝብን ሰላም የሚነሱ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን ለመመከት ሕዝቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጎን በመቆም አስተማማኝ ሰላም መገንባት እንደሚገባው አንስተዋል።
ማኅበረሰቡ ወቅታዊ ሁኔታውን ተረድቶ የክልሉን ሰላም እና ልማት ለማጠናከር በጋራ መምከር እና መሥራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
✍️ በሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።
Next articleመሠባሠቢያ ቤታችን፤ ደምቆ መታያ ውበታችንን እንጠብቅ።