
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት ምሥረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን በድጋሜ የአዲስ አባባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባለፉት ዓመታት አዲስ አበባን በከንቲባነት በመምራት በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን እንደሠሩ ተገልጿል። ውጤታማ
ሥራዎቻቸውን እንዲያስቀጥሉ እና የከተማዋን እድገት እንዲያፋጥኑ በድጋሜ በከንቲባነት እንደተሾሙ ነው የተመላከተው።
