የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት ምስረታ እና የ4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

10
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አሥተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሠብሠቢያ አዳራሽ እያካሄደ ነው።
በጉባዔ ላይ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርን ወክለው የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ተሳታፊ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ጉባኤ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍና እና የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
የከተማ አስተዳደሩን ከንቲባ እና ምክትል ከንቲባ የመምረጥ እንዲሁም የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመትን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Previous articleየኢልኒኖን ተጽዕኖ ለመቋቋም ምን እየተሠራ ነው?
Next articleወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።