
የዜጎችን ምርታማነት በማጎልበት እና ተረጅነትን በዘላቂነት በመቀነስ ረገድ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ በክልሉ የዜጎችን ምርታማነት በማጎልበት ተረጅነትን በዘላቂነት በመቀነስ ረገድ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በምግብ ራስን መቻል ከዓድዋ ቀጥሎ የሀገራችንን ሉዓላዊነት የምናረጋግጥበት የአርበኝነት ግንባር እንደኾነ ነው የገለጹት።
በመኾኑም ምርታማነትን በማሳደግ እና በምግብ ራስን በመቻል ተረጅነትን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተጀመሩ አሠራሮችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ተፈናቃዮችን በዘላቂነት በማቋቋም እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የተመዘገበው ውጤት ከኢኮኖሚ ጥቅም ባሻገር ከሀገራዊ ነጻነት እና ከዘላቂ ልማት ጋር የተያያዘ ትልቅ ጉዳይ መኾኑንም አንስተዋል።
በቀጣይም የዜጎች ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲረጋገጥ የክትትል እና የድጋፍ ሥራን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በክረምት በጎ ፈቃድ ከ210 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉ ተግባተራት መከናወናቸውን ኀላፊው ተናግረዋል።
#ባሕር _ዳር #መስከረም-18_2019 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ!
