
የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ፓትሪክ ቪየራ ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለብዙ ዓመታት በገዛ ሜዳው ጨዋታ ሳያደርግ የቆየ በመኾኑ ጨዋታው ከባድ ሊኾን እንደሚችል ገልጸዋል። ለዚህም ተገቢውን መፍትሔ መፈለግ የእነሱ ሥራ እንደሚኾን ተናግረዋል።
አሠልጣኙ የምንጫወትበት ስታዲየም እና የመጫወቻ ሜዳው ጥራት ለእኛ እጅግ ምቹ በመኾኑ ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ እንወስደዋለን ብለዋል።
ዋና ዓላማቸው ሦሥቱን ነጥብ ማግኘት መኾኑን አንስተዋል። ተጋጣሚያቸውን አክብረው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ እና በመስመሮች መካከል ክፍት ቦታዎችን ለማግኘት በፈጣን የጨዋታ መንገድ እንደሚጫወቱ ገልጸዋል።
ቡድናቸው በተሰጥኦ የተሞላ ቢኾንም የመጀመሪያ ዓላማቸው ይህንን ተሰጥኦ አጣጥሞ ወደ አንድ ጠንካራ የቡድን መንፈስ ማምጣት መኾኑን አብራርተዋል።
በአሁኑ የእግር ኳስ ዘመን ውጤት የሚያመጣው የግል ተሰጥኦ ሳይኾን የቡድን ሥብሥብ ጥራት እንደኾነም ገልጸዋል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_18_2019_ዓ_ም
በጥበቡ ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
