
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በሰላም ግንባታ እና በመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
ውይይቱ ወጣቶች አንድነታቸውን በማጠናከር እና በመደራጀት የአካባቢያቸውን ሰላም እና ጸጥታ ለማስከበር የሚጫወቱትን ሚና ለማሳደግ ያለመ ነው።
በውይይቱ የተሳተፉት ወጣቶች ሰላምን ለማስፈን በመደራጀት እና አንድነታቸውን በማጠናከር ኀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
መንግሥት በበኩሉ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ወጣቶች ከሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመተባበር ለሀገር ሰላም መረጋገጥ በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው በውይይቱ ላይ ተመላክቷል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ ወጣቶች የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ኀላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ የተገኙት የአማራ ክልል መንገድ ኤጀንሲ ምክትል ቢሮ ኀላፊ አስራቴ አለኸኝ ወጣቶች ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ በመረዳት፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት እና ለጸጥታ ኀይሉ አጋዥ በመኾን የሀገርን ሉዓላዊነት እና አንድነት ማስጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
#ደብረ_ማርቆስ #ሰላምና_ጸጥታ #ወጣቶች #አሚኮ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ደብረ_ማርቆስ #መስከረም_18_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
