
የመስቀል በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ አከባበር ላይ አባታዊ ትምህርት አና መልዕክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጽዕ አቡነ ሚካኤል መስቀል የሰው ልጅ የድኅነት እና የነፃነት ምልክት መኾኑን ተናግረዋል።
የአሁኑ ትውልድ የመስቀሉን ረድኤት እና በረከት ለማግኘት በጸሎት መትጋት እንዳለበት ያሳሰቡት ብጽዕነታቸው የድኅነት መሠረት የኾነውን ይህን በዓል ስናስብ በይቅርታ እና በመተሳሰብ መኖር ይገባናል ነው ያሉት።
“እውነትን ፍለጋ የወጣችው ንግሥት ዕሌኒ እውነትን በመያዟ የተቀበረውን መስቀል ማግኘት እንደቻለችው ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያውያን የጠፋውን ሰላም መፈለግ ይገባቸዋል” ብለዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኃይለኢየሱስ ሰለሞን የደብረ ታቦርን ገናና ስም የሚመጥን ሥራ በመሥራት እና የጥበበኞችን ምድር ከፍ አድርጎ በማስቀጠል ረገድ ከአሁኑ ትውልድ ትልቅ ኀላፊነት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
መስቀል የሰላም እና የይቅርታ መገለጫ በመኾኑ ሁሉም በጋራ በመቆም ለሀገር ሰላም መጽናት እንዳለበት ተናግረዋል።
#አሚኮ #መስቀል #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ደብረ_ታቦር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ተክለብርሃን ፈንታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
