የመስቀልን በዓል በምሥጋና፣ በፍቅር፣ በይቅርታ እና በአንድነት ማክበር ይገባል።

6

 

የመስቀል በዓል በጎንደር ከተማ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ዮሴፍ ደስታ የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ለየት የሚያደርገው የቤተክርስቲያን ጥያቄዎች በተመለሱበት ወቅት መከበሩ ነው ብለዋል።

በዚህም የመካነ ሕይዎት ፊት አቦ፣ ደብረ ምጥማቅ ማርያም እና የቅዱስ ዮሐንስ አብያተ ክርስቲያናት የቦታ ጥያቄዎች መልስ አግኝተዋል ነው ያሉት።

ጎንደር ከ100 ዓመታት በላይ ልማት ርቋት ቆይቷል ያሉት ዋና ሥራ አሥኪያጁ አሁን የተሠሩ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ውብ አድርጎታል ብለዋል።

ይህን ላደረጉ ለፌዴራል፣ ለክልል እና ለከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ምሥጋና አቅርበዋል።

የመስቀል በዓል በምሥጋና፣ በፍቅር፣ በይቅርታ እና በአንድነት ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል።

በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ የሃይማኖት አባቶች የጸጥታ አካላት፣ የስንበት ትምህርት ቤት አባላት እና አማኞች ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

#አሚኮ #መስቀል #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ጎንደር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አዲስ ዓለማየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎የመስቀል ደመራ በዓል በሞጣ ከተማ በሃይማኖታዊ ሥነ- ሥርዓት ተከበረ።
Next article“እንደ ንግሥት ዕሌኒ እውነትን በመያዝ የጠፋውን ሰላም ልንፈልግ ይገባል” ብጹዕ አቡነ ሚካኤል