
በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አሥተዳደር የመስቀል ደመራ በዓል በዛሬው ዕለት በሰባቱ ዋርካ መስቀል አደባባይ በድምቀት ተከብሯል።
የከተማዋ ከንቲባ ተመስገን ዘውዴ የደመራውን በዓል ስናከብር፣ በመስቀሉ የተደረገው እርቅና እና የተገኘው ሰላም በሁላችን ልብ መገኘት ይኖርበታል ብለዋል። መስቀል የትዕግሥት፣ የእርቅ እና የሰላም ምልክት መኾኑን ዘወትር ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች ዛሬም እንደትናንቱ በከተማችን የሚከናወኑ የልማት እና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎችን እውን ለማድረግ ሰላም እና ፀጥታ ማረጋገጥ ወሳኝ በመኾኑ ከጥምር ጦራችን ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የሞጣ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የመፅሀፍ መምህር ክበር ተመስገን የመስቀል ደመራ በዓል አንድነት እና መተሳሰብ በሚጎለብቱበት፣ ሃይማኖታዊ እና የባሕል እሴቶች በድምቀት የሚፀባረቁበት ሲሆን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል።
የሃይማኖቱ ተከታዮች በበኩላቸው የመስቀልን በዓል ስናከብር ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
#አሚኮ #መስቀል #ሞጣ #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
