
የመስቀል በዓል በጎንደር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሣ ጎንደር የኢትዮጵያ ጥንታዊነት እና ታሪካዊነት ጎልቶ የሚወጣባት ከተማ ናት ብለዋል። ጎንደር የፋሲል አብያተ መንግሥታትን ጨምሮ ሌሎች ታሪኮች በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ ያደረገች ከተማ መኾኗን ተናግረዋል።
በዩኔስኮ የተመዘገበውን የመስቀል በዓል በጥንታዊቷ ጎንደር ከተማ ማክበር ልዩ እንደሚያደርገው ነው የገለጹት። በዓሉን ከሃይማኖታዊ ትውፊቱ ባሻገር የቱሪዝም መዳረሻነቱም እንዲስፋፋ አሁን ካለው በላይ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚገኙ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በማልማት በኩል በትኩረት እየሠራ ይገኛል ነው ያሉት።
የጎንደር ጥንታዊነት ከአባቶች ዝማሬ እና ከወጣቶች መዝሙር ባሻገር የምዕመናን አለባበስ ቀልብን የሚስብ መኾኑን አንስተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የከተማዋ ውበት ለጎብኝዎች ምቾትን የሚፈጥር ነውም ብለዋል።
#አሚኮ #መስቀል #Ethiopian ✝️🇪🇹
#ጎንደር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም
✍️ በደስታ ካሣ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
