የመስቀል በዓል በላሊበላ

2

 

የመስቀል በዓል በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ተከብሯል።

የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አሥተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ የመስቀል በዓል አከባበር በቅዱስ ላሊበላ ለዘመናት በልዩ ሁኔታ ሲከበር መቆየቱን ገልጸዋል።

የመስቀል በዓል አከባበር ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ መምጣቱን እና በዓሉ በቅዱስ ላሊበላ ልዩ የአከባበር ይዘት እንዳለውም አንስተዋል።

ቅዱስ ላሊበላ መስቀልን በውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ በልዩ ልዩ ምልክት አስቀምጦታል ብለዋል።

የቅዱስ ላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፈንታው አባተ የመስቀል በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የሰው ልጆች የመዳን ምስጢር የተገለጸበት መኾኑን ገልጸዋል።

በዓሉ የአንድነት እና የኅብረት መኾኑ አንስተዋል። የበዓሉ መከበር ትርጉሙ የላቀ ነው ብለዋል።

ከላሊበላ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በዓሉን ስናከብር መረዳዳትን እና መደጋገፍን በማስቀጠል ሊኾን ይገባል ነው ያሉት።

Previous article🔥”አንድ እንጨት ብቻውን አይበራም፤ ጨለማውን የምንገፈው ስንደመር ነው!”