ለጽኑ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የማይናወጥ መሠረት የጣለች ባለ ራዕይ ሀገር- ኢትዮጵያ🇪🇹

3

 

ኢትዮጵያ በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በትውልድ ቅብብሎሽ የተገኙ ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት ለጽኑ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የታላቅ ሕዝቦች መኖሪያ እና ባለርዕይ ታላቅ ሀገር ናት። ለልህቀት እና ለዜጎቿ ክብር አስባ ነገዋን በመሥራት ላይም ትገኛለች። የሁሉንም ዜጎች ሕይወት ከሚለውጡ ሰው ተኮር የኮሪደር ልማቶች፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን በተግባር እውን አድርጋ ለዓለም አሳይታለች።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል ብለዋል።

“እኛ የምንገነባው አካታች የኾነች፤ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፤ የአብሮነት እና መረዳዳት ባሕል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይኾን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነት እና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን” ሲሉም በአዲስ ዓመት ዋዜማ መልዕክታቸው አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ እውነትም ትልቅ ሀገር፣ የትልቅ ሕዝብ መኖሪያ እና ባለርዕይ መኾኗን ዓለም በውል ያውቀዋል። እኛም ልጆቿ በአንድነት ቆመን ለሀገራችን ክብር የሚመጥኑ ሥራዎችን ማከናወን እና ከፍታዋን ማብሠር የዘወትር ሥራችን ሊኾን ይገባል።

#ባሕር_ዳር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🔥 የደመራው ፍም እና የሰላም ብርሃን🕊️
Next article🌼 “የት እንደከረመች አትጠየቅም፤ ወዴት እንደምትሰወርም አይታወቅም”🕊️