🇪🇹“ኢትዮጵያ ታምርት”፦ የትልቅ ሀገር፣ የትልቅ ሕዝብ ታላቅ ርዕይ!

8

​
የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን ተከትሎ የተቀረፀው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ በሀገራችን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ አዲስ ህይወት በመዝራት ረገድ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
​ንቅናቄው ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙ ማቆልቆሎችን በመቀየር፣ የአምራች ዘርፉን አቅም ወደ አዲስ ደረጃ አሸጋግሯል።

​የንቅናቄው ዋና ዋና ስኬቶች፦
🎯የማምረት አቅምን ማሳደግ፦ በፋብሪካዎች ይባክን የነበረውን የማምረት አቅም (Capacity Utilization) በማሻሻል፣ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

🎯የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት፦ ከውጭ ሀገር በውድ የውጭ ምንዛሬ ይገቡ የነበሩ በርካታ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በስፋት በማረት፣ የውጭ ምንዛሬን ማዳን ተችሏል።

🎯የስራ ዕድል ፈጠራ፦ ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች፣ አስተማማኝና ዘላቂ የስራ ዕድል ፈጥሯል።

🎯ኢንቨስትመንትን መሳብ፦ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች የተሻለና ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር በመፍጠር አዳዲስ ፋብሪካዎች እንዲከፈቱ መንገድ ጠርጓል።

​“ኢትዮጵያ ታምርት” የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን በራሷ ምርትና አቅም እንድትቆም የሚያስችል የነገዋ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ ጠንካራ መሠረት ነው።

​#ኢትዮጵያታምርት #EthiopiaTamrit #EthiopianEconomy #HomeGrownEconomicReform
#ባሕር_ዳር፡ መስከረም 17/2019 ዓ.ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article«የመስቀል በዓል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን የዓለም ታላቅ ሃብት ነው» ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
Next articleየገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፦ የኢትዮጵያ የቱሪዝም እና የልማት አዲስ ምዕራፍ።