
የመስቀል በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች መዝገብ የተመዘገበ እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ታላቅ የአደባባይ በዓል ነው።
በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የደመራ በዓል ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ጎንደር ዞን አሕጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት በዓሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይኾን የመላው ዓለም ታላቅ ሃብት መኾኑን አብራርተዋል።
ይህንን የዘመናት ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ እሴት የተላበሰ በዓል መጠበቅ እና መንከባከብ ከአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅ ታላቅ ኀላፊነት መኾኑን አሳስበዋል።
በዕለቱ በተካሄደው የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር እና የደቡብ ጎንደር ዞን የሥራ ኀላፊዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት በዓሉ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
#አሚኮ #መስቀል #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ደብረ_ታቦር #መስከረም_16_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ፦ተክለብርሃን ፈንታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
