“መስቀል ኢትዮጵያን ለዓለም የገለጠ ሃይማኖታዊ እሴት ነው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

5

 

የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበዓሉ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በመዲናዋ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የኾነው የመስቀል በዓል ለዘመናት ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ፤ እና ደምቆ ሲከበር የኖረ ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ወደር በማይገኝለት ፍቅር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ የሰጠበት እውነት መኾኑንም ገልጸዋል።

በዓሉን ስናከብር ክርስቶስ የሰጠንን ያንን ፍቅር ያለምንም ልዩነት በፍቅር እና በይቅርታ ታሳቢ እያደረግን ሊኾን ይገባል ነው ያሉት። ይህንን ስናደርግ የምንዋደድ፣ ይቅር የምንባባል እና ሰላም ያለን እንኾናለን ነው ያሉት።

በዓሉ ለዘመናት ሲከበር ሁለንተናዊ ፋይዳዎችን አቅፎ ነው ያሉት ከንቲባዋ በዩኔስኮ ተመዝግቦ በዓለም ላይ ባሕላዊ ሃብታችንን እና ገጽታንችንን ከፍ ያደረገ የጋራ እሴታችን መኾኑንም ተናግረዋል።

#አሚኮ #መስቀል #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_16_2019_ዓ_ም

✍️ በአድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ወቅቱ የእርቅ መንፈስን የሚጠይቅ በመኾኑ ያለፈውን በይቅርታ አልፎ አንድነትን ማጠናከር ይገባል” አቶ ጎሹ እንዳላማው
Next article“የመስቀሉ መገለጥ ለዓለም ደኅንነትን፣ ፍቅርን እና ሰላምን ይዞ የመጣ ነው” ብጹዕ አቡነ ቶማስ