
የሰሜን ሸዋ ዞን ፍትሕ መምሪያ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል የመልካም ምኞት መልዕክቱን አስተላልፏል።
መምሪያው በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲኾን እየተመኘ ፍትሕ እና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ዞን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁልጊዜም ከሕዝቡ ጎን በመኾኑን እንደሚሠራ አረጋግጧል።
መምሪያው የወንጀል ምርመራዎችን በመከታተል፣ የመንግሥት እና የሕዝብ ጥቅምን በማስጠበቅ፣ የሕግ ግንዛቤን በማስፋት እና ነፃ የሕግ ድጋፍ በመስጠት ረገድ ባከናወናቸው ያልተቋረጡ ጥረቶች በ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በክልል ደረጃ አንደኛ በመውጣት ከፍተኛ ዕውቅና ማግኘቱን አስታውሷል።
በተጨማሪም በዞኑ ደረጃ አገልግሎትን በማዘመን እና ተገልጋይን ማዕከል ያደረገ ፈጣን አሠራር በመዘርጋት ከዞኑ መምሪያዎች ቀዳሚ ኾኖ ማጠናቀቁ ተገልጿል።
መምሪያው በቀጣይም ፍትሕን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እና የሕግ የበላይነትን ለማጽናት በላቀ ቁርጠኝነት እንደሚሠራ ነው የተገለጸው።
#አሚኮ #የደመራ_በዓል #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
#ደብረ_ብርሃን #መስከረም_16_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
