” የመስቀል በዓል እውነት የተገለጠበት፣ የኅብረት እና የትብብር ምልክት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

9

 

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የመስቀል በዓል ተስፋ እና ብርሃን የታየበት፣ እውነት የተገለጠበት፣ የኅብረት እና የትብብር ምልክት ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል ልዩነቶችን በይቅርታ ተሻግረን በአብሮነት የምናከብረው የአንድነታችን ማሳያ ነው። ተራርቀው የቆዩ ወዳጅ ዘመዶች የሚገናኙበት ክብረ በዓል ነው።

የመስቀል ብርሃን የተገለጠው በሦስት መቶ መታት ጽናት እና በወራቶች ያልተቋረጠ ትዕግስትና ትጋት ነው። ይሄውም ራዕያችን እውን የሚኾነው ለእውነት በጽናትና በትዕግስት ጥረት ማድረግ ስንችል መኾኑን ያስረዳናል ነው ያሉት። ዛሬም ለጋራ ሰላማችን፣ ለሀገራችን ልማት እና ብልጽግና በትብብር መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።

የደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ሕዝባችን ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪዬን አቅርባለሁ ነው ያሉት። በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲኾንም ተመኝተዋል።

Previous article✝️ የጽናት ምልክቷ፦ ንግሥት ዕሌኒ
Next articleበዓሉ የበጎነት፣ የመልካምነት እና የሰላም ይሁንላችሁ” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ