‎‎”አስቸጋሪ የክረምት ወር አልፎ የመጸው ወር በሚብትበት ጊዜ የሚከበረው መስቀል የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ነው፡፡” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

9

‎
‎ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፦
‎
‎እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!
‎
‎የመስቀል በዓል መስቀሉ ለ300 ዓመታት ከተደበቀበት የወጣበት በዓል ነው፡፡ መልካም የምሥራች የተነገረበትና ብርሃን የተገለጠበት በዓል ነው፡፡ በአንድ ዘመን የተሳሳቱ ሰዎች የፈጠሩትን ጥፋት፤ በሌላ ዘመን የተነሡ ተቆርቋሪ ሰዎች አስተካክለውታል፡፡ ልክ እኛ የባሕር በርን ለማስተካከል እንደምንሠራው፡፡
‎
‎አስቸጋሪ የክረምት ወር አልፎ የመጸው ወር በሚብትበት ጊዜ የሚከበረው መስቀል የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ነው፡፡ በአንድ በኩል ችቦዎች ተደምረው ደመራውን ይገነባሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ሁሉ በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ አከባበር፤ እንደየብሔረሰቡ ባሕል ተደምረው በዓሉን ያከብራሉ፡፡
‎
‎“የጎመን ምንቸት ውጣ፣ የገንፎ ምንቸት ግባ” እንደሚባለው ሁሉ፣2019 ዓመት፣ አስቀድሞ መውጣት የጀመረው የኢትዮጵያ የችግርና የፈተና ምንቸት ተጠቃልሎ የሚወጣበትና የብልጽግና ምንቸት በየቤታችን የሚገባበት ዓመት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

‎መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁን፡፡
‎
‎#አሚኮ #መስቀል_በዓል #ኢትዮጵያ🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #መስከረም_16_2019_ዓ_ም
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article✝️ ከመንፈሳዊ በዓልነት እስከ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ።
Next article“የተሰቀለውን ያመልካሉ፤ የተሰቀለበትንም ያከብራሉ”