
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባሕላዊ በኾነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል መኾኑን ገልጸዋል። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ ዓደባባይ ይተምበታል ነው ያሉት።
ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።
በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብን እና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ ብለዋል።
በዓሉ መልካም በዓል እንዲኾንም ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም
