ጦም የሚያድር መሬት አይኖርም።

2

 

በወልድያ ከተማ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመረው ንቅናቄ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመረውን ንቅናቄ ለማሳካት የወልድያ ከተማ አሥተዳደር በዘመቻ መልክ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አስናቀች ኀይሌ እንደገለጹት ከተማዋ ከውጭ እርዳታ እና ተረጅነት በመላቀቅ የራስን አቅም በመጠቀም የማምረት አቅምን ለማሳደግ እየሠራች ነው።

በከተማዋ ከ29 ሺህ በላይ ተረጂዎች መለየታቸውን ገልጸዋል። ከተረጂዎች እስከ መሪ እና የመንግሥት ሠራተኛው ድረስ የተረጅነትን አጸያፊነት የሚያስረጽ ሕዝባዊ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ተከናወኗል ብለዋል።

አቅም የሌላቸው ተረጂዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሥራ አጥ ወጣቶች በልብስ ስፌት፣ በዶሮ እርባታ፣ በሌሎች የአገልግሎት እና አምራች ዘርፎች ተሰማርተው ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩም እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

በከተማዋ ለድንገተኛ አደጋ እና የመሥራት አቅም ለሌላቸው ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረስ የሚያስችል የእህል ክምችት በመጋዘን እየተሠባሠበ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ እታገኘሁ አደመ ከተረጅነት ለመላቀቅ በየትኛውም የሥራ መስክ ውጤታማ መኾን አና የሥራ ባሕልን ማዳበር አስፈላጊ መኾኑን ለአሚኮ ገልጸዋል።

ወልድያ ከተማ “ጦም የሚያድር መሬት አይኖርም” በሚል መርህ የተቋማትን መሬት በአዝመራ በመሸፈን የእርዳታ መጋዘኖችን ለመሙላት እያደረገች ያለውን ተጨባጭ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የከተማዋን አቅም እና ጸጋ በመለየት የተጀመረው ይህ ተሞክሮ በሌሎች አካባቢዎችም ሊሰፋ እንደሚገባ አሳስበዋል።

#Woldia #Amhara #Ethiopia #Productivity #AMICO🇪🇹

#ወልድያ #መስከረም_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየይለፍ ቃልዎ ጠንካራ ነው ወይስ? ምንስ ሊገጥመዎት ይችላል?
Next article‎በጃናሞራ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።