
ባሕር ዳር: መስከረም 15/2019 ዓ.ም (አሚኮ) ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም የኢሜይል፣ የባንክ እና የማኅበራዊ ሚዲያ መለያዎችን ከሳይበር አጥቂዎች፣ ከማንነት መዘረፍ እና ከፋይናንስ አደጋ ይጠብቃል።
ነገር ግን በርካታ መለያዎችን በጭንቅላት ማስታወስ ስለሚከብድ፣ ውስብስብ ምልክቶችን በየጊዜው መጻፍ ስለሚያሰለች እና “እኔ ላይ የሳይበር ጥቃት አይደርስም” በሚል የተሳሳተ እምነት ምክንያት፣ ብዙዎች ከጠንካራ የይለፍ ቃል ይልቅ ቀላሉን ይመርጣሉ።
እና እንደ ስም፣ የልደት ቀን ወይም «123456» ያሉ ተገማች የይለፍ ቃላትን መጠቀምም በስፋት የተለመደ ነው። ኢንሳ እነዚህ ቀላል ምርጫዎች ለመረጃ መንታፊዎች ምቹ ናቸው ይላል።
ከስምንት እስከ አሥራ ሁለት እና ከዚያ በላይ የኾኑ ትልልቅና ትናንሽ ፊደላትን፣ ቁጥሮችን፣ ልዩ ምልክቶችን ማለትም @, #, $ ያካተተ ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም ተገቢ ነው።
በተጨማሪም ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) መጠቀም የሳይበር ጥቃት አደጋን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
-በመኾኑም እየሰፋ ከመጣው የሳይበር ጥቃት ራስን ለመከላከል ጠንካራ እና የማይገመት የይለፍ ቃልን መጠቀም የመከራል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
