
ርእሰ መሥተዳድሩ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ እና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ማበረታቻ እና ድጋፍ አድርገዋል።
በክልሉ በፈተናው ከ500 በላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ሰሞኑን የተበረከተ ሲኾን ዛሬ ደግሞ ከከተማ እና ከገጠር ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ እና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች እገዛ ተደርጎላቸዋል።
ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ውጤታማ ተማሪዎችን መሸለም እና መደገፍ ሥነ ልቦና ከመገንባቱም በላይ ለሌሎች ተማሪዎች ትልቅ አርዓያ ይኾናል።
ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ቆይታቸው በትጋት በመማር የተለመደ ስኬታቸውን ማስቀጠል እንዳለባቸውም ርእሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል። የክልሉ መንግሥት ለትምህርት ዘርፉ እና ለተማሪዎች የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
#አሚኮ #የትምህርት_ድጋፍ #ሀረሪክልል_ኢትዮጵያ
#ባሕር_ዳር #መስከረም_15_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
