
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ገደብጌ እና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የወገራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሹመት ዋሴ መንግሥት የሰላም አማራጩን ክፍት በማድረግ በግጭት ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ዕድል እየሰጠ መኾኑን ገልጸዋል ።
የወገራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አይፈራም አያናው የማንም ተላላኪ ላለመኾን የሰላም አማራጭን መከተላችሁ ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከለካያ ሠራዊት
አዛዦች ሰላምን መምረጥ ለግለሰቦችም ኾነ ለማኅበረሰቡ ዘላቂ ጥቅም ያለው ውሳኔ መኾን ገልጸዋል። ታጣቂዎች የሰላም አማራጩን በመቀበላቸው አድንቀዋል።
ከወገራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች በትጥቅ ትግል ሳይኾን በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል በመገንዘብ የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ገልጸዋል።
