በአዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ይፋ ኾነ።

54
ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመኾን በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የኾነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታን ዛሬ ይፋ አድርገናል።
‎
‎ ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች ላይ በሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎች የተደገፈ መኾኑን ገልጸዋል። ይህ ታሪካዊ መሰረተ ልማት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር ነው።
‎
‎የሎጂስቲክስ ወጭን እና መዘግየትን በመቀነስ የኢነርጂ ዋስትናን ያጠናክራል፤ የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የንግድ መስመርን ፍጥነት እና ዘላቂነትን ያሳድጋል ብለዋል።
‎
‎መሰረተ ልማቱ ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ በላይ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንት እና በጋራ መልማትን ማዕከል ያደረገ፣ ለዘላቂ እድገት፣ ለቀጣናዊ ትስስር እና ይበልጥ አስተማማኝ ለኾነ የጋራ ኢኮኖሚያዊ እጣ ፈንታ የሚደረግ ሰፊ ኢንቨስትመንት ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
Previous article“ከተለዋዋጭ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመሻገር አቅምን ማሠባሠብ ይገባል”
Next article“ተፈጥሯዊው የኢትዮጵያ አምባሳደር”