
የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 35ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። የብሔረሰብ ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሙሉአዳም እጅጉ
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የታቀዱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ዕቅዶች ተፈጻሚ እንዲኾኑ ምክር ቤቱ ክትትል እና ቁጥጥር ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም መልካም አፈጻጸም ተመዝግቧል ነው ያሉት።
ወቅቱ እጅግ ተለዋዋጭ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች የሚስተዋሉበት ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ
ከፈተና ለመሻገር በችግሮቻችን ምልከታ ላይ የጋራ አረዳድ መፍጠር እና አቅምን ማሠባሠብ ይገባል ብለዋል።
የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ወድነትን ማረጋጋት እና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ በቀጣይ በትኩረት መፈጸም የሚገባቸው ተግባራት መኾናቸውንም አስገንዝበዋል
የምክር ቤት አባላት ለመሠረታዊ ጉዳዮች ተፈጻሚነት የሕዝብ ውክልናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
