‎ባሕር ዳር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅታለች።

32

‎
‎የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደረሽን (ካፍ) ባወጣው ይፋዊ መርሃ ግብር መሰረት በዚህ ዓመት መስከረም 19/2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር በሀገር ውስጥ እንደሚደረግ አስታውቋል።

‎ይህን ታላቅ ዓለም አቀፍ ጨዋታ በደመቀ ሁኔታ ለማስተናገድ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የተመረጠ ሲሆን ዝግጅቶችም ተጠናቀዋል። ይህን ተከትሎ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶችን፣ ተጫዋቾችንና የስፖርት አፍቃሪያንን ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
‎
‎ውድድሩን ለመመልከት ወደ ውቢቷ ባሕር ዳር የሚመጡ እንግዶች በጣና ሐይቅ እና በዓባይ ወንዝ ዳርቻ ዙሪያ፣ እንዲሁም ውብ በሆነችው የባሕር ዳር ከተማ የማይረሳና ጥሩ ጊዜ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል።እንደዚህ አይነት ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በባሕር ዳር ከተማ መካሄዳቸው የከተማዋን ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ ዕድል ነው።
‎
‎ቢሮው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) መልካም ዕድል ተመኝቷል።
‎
‎#አሚኮ #ኢትዮጵያ #ብሔራዊ_ቡድን #ባሕርዳር_ስታዲየም
‎
‎#ባሕር_ዳር: መስከረም 14/2019 ዓ.ም
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous articleሰው ሰራሽ አስተውሎት ​ለጤናው ዘርፍ ተስፋ ወይስ ስጋት?
Next article💻 ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሚውል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።